Get Mystery Box with random crypto!

'የፒያኖዋ እመቤት' እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ አረፉ። መጋቢት 18፣ 2015 በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ | Ethio Book Review

"የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ አረፉ

መጋቢት 18፣ 2015

በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቫዮሊን እና ፒያኖ አቀናባሪ “የፒያኖዋ እመቤት” እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ በ99 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

እማሆይ ፅጌማርያም ከአባታቸው ገብሩ ደስታ እና እናታቸው ካሣዬ የለምቱ በ1916 በአዲስ አበባ ውስጥ የተወለዱ ሲሆን፤ በልጅነታቸው ለትምህርት በሄዱባት ስዊዘርላንድ ፒያኖን በደንብ ተምረዋል።
በ19 ዓመታቸው ወደ ወሎ ግሸን ማርያም ገዳም በመሄድ በ21 ዓመታቸው ምንኩስናን ተቀብለዋል።

ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም የውብዳር ሲሆን፤ በወጣትነታቸው ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ መጠሪያቸው ወደ እማሆይ ፅጌማርያም ተቀይሯል።
ከ1984 ጀምሮ ኑሯቸውን በእየሩሳሌም አድርገዋል።

አባታቸው ገብሩ ደስታ የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩ ሲሆን፤ በአፄ ሃይለስላሴ ዘመንም የፓርላማ አፈ ጉባኤ በመሆን ማገልገላቸውን የቤተሰባቸው ታሪክ ያስረዳል።

እማሆይ ፅጌ ማርያም እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ፣ ዕብራይስጥኛ፣ አማርኛ ና ግዕዝን አቀላጥፈው የሚናገሩ ሲሆን፤ የተለያዩ የሙዚቃ ሥራዎቻቸው በማቅረብ የሚገኙትንም ገንዘብ ለድሆች መርጃ አውለዋል።

እማሆይ ፅጌማርያም ከሰሯቸው ከበርካታ የሚዚቃ ሥራዎች ውስጥ « Homeless Wonder » /ሆምለስ ወንደር/ ፣ «The Son of Seam» /ዘ ሰን ኦፍ ሲም/፣ «The Mad Man's Daughter» /ዘ ማድ ማንስ ዶተር/ እና «Mother's Love» /ማዘርስ ላቭ/ የሚል አርዕስት ያላቸው ሙዚቃዎች ከበርካታ ሥራዎቻቸው ውስጥ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ።

እማሆይ ፅጌማርያም በሙዚቃ መሳርያ ብቻ የተቀናበሩ ረቂቅ ሙዚቃ በመጫወት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት መሆናቸውም ይነገርላቸዋል።

"ማንበብ ፋሽን ነው።"