Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ ' እስረኞቹ ' እንዳለጌታ ከበደ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለ | Ethio Book Review

አዲስ መጽሐፍ ጥቆማ
" እስረኞቹ "
እንዳለጌታ ከበደ

ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ብዙዎች ተገስጸዋል፣ በገንዘብ ተቀጥተዋል፤ ከደረጃቸው ዝቅ ተደርገዋል፤ ተሰደዋል፤ ታስረዋል፤ለሞት ተላልፈው ተሰጥተዋል። ደግሞም በየዘመናቱ የታሰሩ ከያኒዎች እና ጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆኑ የታሰሩ ሃሳቦችም አሉ። ለጊዜው ወይም ለዘለቄታው <ተወሽቀው> የተቀመጡ። የታሰረው ወይም የሚታሰረው ግለሰብ ብቻ አይደለም፡፡ ግለሰቡ ሲያስበው የነበረው ሃሳብ ብቻም አይደለም፡፡ አሳሪውም ታሳሪ ነው፤ <ደግሞ መጡብኝ> ብሎ ራሱን አሳስሮ የተገኘ . . .በነጻነት የተገለጸውን ሃሳብ ምን መዘዝ ያስከትልብኝ ይሆን? ብሎ በመሳቀቅ ዘመኑን የፈጀ . . .

እና ይህ መጽሐፍ ስለእነዚህ እስረኛ ስለነበሩ ግለሰቦች፣ እስረኛ ስለሆኑ ሃሳቦች እና <አሳሪዎቻቸው> ይተርካል፣ እያሳቀም፣ እያሳቀቀም ፤ እያስለቀሰም ፣ እያጫወተም ፣ እያጨዋወተም. . . <ነበር>ን እና <ነው>ን
ያወጋል።