Get Mystery Box with random crypto!

የሶፍትዌር ችግር ማለት ምን ማለት ነው? ከሚከተሉት አንደኛው ወይም ሁሉም ችግሮች በአይፎን ወይም | Mobile

የሶፍትዌር ችግር ማለት ምን ማለት ነው?

ከሚከተሉት አንደኛው ወይም ሁሉም ችግሮች በአይፎን ወይም የአንድሮይድ ስልክዎ ላይ ተከስተው ያውቃሉ? ስልክዎ በራሱ ጊዜ እየበራ ይጠፋል፣ ወይም Involuntary Restart ያደርጋል ስልኩ ሙሉ በሙሉ አይነሳም Dead Phone ይሆናል ከጫኗቸው አፕሊኬሽኖች የተወሰኑቱ ተለይተው ያለመስራት ወይም የመዘግየትና ስታክ የማድረግ ችግር ያሳያሉ በአጠቃላይ ስልክዎ እጅግ በጣም ቀርፋፋ ይሆናል ( በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ይህ አይነቱ ችግር በስልካችን ላይ በጣም ብዙ አፕሊኬሽኖችና ዳታዎችን በመያዝ ምክንያት ከሚሞሪ መጣበብም የተነሳ ሊከሰት ይችላል) ወይም የአንድሮይድ ወይም የአፕል ሎጎ ላይ Stack ያደርጋል ለስልክዎ ያስገቡት የፓተርን ፓስወርድ ጠፍቶዎታል፣ ወይም User Locked ሆኗል የኔትወርክ መዘጋት(Carrier Network Locked )፣ ከሚከተሉት አንደኛውን መልእክት ይሰጥዎታል SIM not Valid, Wrong SIM, Contact SP (Service Provider), Unknown SIM, Phone Restricted ወዘተ…
እና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ ስልኩ የሶፍትዌር ችግር አለው ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ከዚህ በታች የሚከተሉት መፍትሄዎች ችግሩን ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ እፎይታ ይሰጡዎታል ማለት ነው ማሳሰቢያ፡- ማንኛውንም የሶፍትዌርም ሆነ የሀርድዌር ጥገና ከመከወናችን በፊት data backup ማድረግ ወይም ያሉንን ዳታዎችና መረጃዎች ወደሌላ ሚዲየም (ወደሌላ ፍላሽ ሚሞሪ ወይም ወደ ኮምፒውተር ወይም ወደጎግል ወይም አይክላውድ አካውንት) ማዛወር ይኖርብናል፡፡ ይህን ማድረግ በጥገናው ሂደት ለሚደርስ የዳታ መጥፋት ሁነኛ መፍትሄ ይሆናል፡፡ ለአንድሮይድ ስልኮች Hard Reset or Factory Reset ማድረግ Format ማድረግ በዚህም ችግሩ ካልተፈታ በ Stock Firmware Flash ማድረግ Unlocking, Android Rooting ማድረግ (User, Network Provider or Carrier etc… ) እና ሌሎችም ለአይፎን ስልኮች በቅርብ ጊዜ የ iTunes Software Restore ማድረግ ቀደም ብለው በነበሩት የአይፎን ስልኮች ላይ የተለያዩ የJailbreaking ሶፍትዌሮች በመጠቀም የኔትወርክ ክልከላውን ሰብሮ ማለፍ እና ሌሎችም በድጋሚ ማንኛውንም የሶፍትዌርም ሆነ የሀርድዌር ጥገና ከመከወናችን በፊት data backup ማድረግ በፍጹም በፍጹም
እንዳይዘነጉ፡፡

http://t.me/mobilerepair11