2021-09-04 09:56:36
#የሞባይል_ድምፅ_ጥገና
===================
የሞባይል ድምፅ ችግር በ6 የተለያዩ ክፍሎች የሚከፈል ሲሆን መፍትሄዎችም እንደሚከተለው ይቀርባል።
1. #እኛ_የምናወራው_ድምፅ_አይሰማም
#መፍትሄ
መጀመሪያ የስልካችን ማይክ በአይናችን እናየዋለን። የተሰበረ ወይም የተጣመመ ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ ይገባል። ማፅዳትም አስፈላጊ ነው።
ከተበላሸ ደግሞ መቀየር ነው። ይሰራል አይሰራም የሚለው በባለሙያ በመልቲ ሜትር ችክ ይደረጋል።
2. #ሌላ_ሰው_የሚያወራው_ድምፅ_አይሰማም
#መፍትሄ
ስፒከሩን በአይናችን ማየት እንዲሁም ይዞታውን ማረጋገጥና የታጠፍ ከሆነ ማስተካከል።
ተሰብረው ከሆነ ደሞ መቀየር ያስፈልጋል።
ስፒከሩን በሚገባ ማፅ ምዳትም ተገቢ ነው ።
3. የጥሪ_ደምፅ_አይሰራም
#መፍትሄ
ሙዚቃ ሲያጫዉቱ አይሰማም፣ ላውድ ስፒከር ላይ አይሰማም፣ ወዘተ የመሳሰሉት ችግሮች #ከሪንገር ጋር በቀጥታ ይገናኛል።
የሪንገሩን ኢንተርፌስ ማፅዳት
ሪንገሩን በአይናችን በማየት ሁለቱ የሪንገር ጫፎች ታጥፈው ወይም ተሰብረው ከሆነ ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
4. #የምንልከው_ወይም_የምንቀበለው_ድምፅ_ይንጫጫል
#መፍትሄ
ማይክን ወይም ስፒከርን በማስተካከል ካልተስተካከለ ችግሩ የማይክ ወይም የስፒከር ማስተላለፊያ መንገድ ላይ ያለው ኢንዳክተር የማጣራት ሂደት ሲቋረጥ ስለሆነ ተገቢውን ማስተካከያ ማድረግ ነው።
5. #ቀፎው_የሄድፎን_ምልክት_ያሳያል
#መፍትሄ
ሴቲንግ ውስጥ በመግባት ሄድፎን የሚለውን ማጥፋት
የሶፍትዋየር ችግር ከሆነ ደግሞ ስልኩን ፎርማት ማድረግ ያስተካክለዋል።
የሀርድዌር ችግር ከሆነ ደግሞ ማይክ አካባቢ በቲነር ማፅዳት ያስተካክለዋል።
ሀድፎን መሰኪው ጋር ያሉ ሽቦዎች እርስበርስ ወይም ደግሞ ከአቃፊው ብረት ጋር ከተገናኙ መርፌን በመጠቀም ማላቀቅ ያስተካክለዋል።
6. #የምንናገረው_ድምፅ_ያስተጋባል
#መፍትሄ
ይህ ማለት የገድል ማሚቶ የሚባለውን ድምፅ የሚያሰማን ከሆነ
http://t.me/mobilerepair11
897 viewsedited 06:56