Get Mystery Box with random crypto!

ለመጸለይ ከፀሐይ ጋር ተነስ። ብቻህን ጸልይ። ብዙ ጊዜ ጸልይ። ብትናገር እግዚአብሔር ይሰማል። | Ethio Book Review

ለመጸለይ ከፀሐይ ጋር ተነስ። ብቻህን ጸልይ። ብዙ ጊዜ ጸልይ። ብትናገር እግዚአብሔር ይሰማል።

በመንገዳቸው የጠፉትን ታገስ። ድንቁርና፣ ትዕቢት፣ ቁጣ፣ ቅናት እና ስግብግብነት የሚመነጩት ከጠፋች ነፍስ ነው። ምሪትን እንዲያገኙ ጸልይ።

ራስህን በራስህ ፈልግ። ሌሎች መንገድህን እንዲያበጁልህ አትፍቀድ። የአንተ መንገድ የአንተ መንገድ ብቻ ነው። ሌሎች አብረውህ ሊራመዱ ይችላሉ፤ ነገር ግን ማንም የአንተን መንገድ ሊሔድልህ አይችልም።

ለእንግዳ ዋጋ ስጥ። በጣም ጥሩውን ምግብ አቅርብላቸው፤ ጥሩውን አልጋ ስጣቸው እና በአክብሮት ያዛቸው።

ያንተ ያልሆነውን ከሰው፣ ከማህበረሰቡ፣ ከበረሃም ሆነ ከባህል አትውሰድ። ካላገኘህ ወይም ካልተሰጠህ ያንተ አይደለም።

በዚህች ምድር ላይ የተቀመጡትን ነገሮች ሁሉ አክብር- ሰዎችም ይሁኑ ተክሎች።

የሌሎችን ሃሳቦች፣ ምኞቶች እና ቃላት አክብር። ሲያወሩ በፍፁም አታቋርጥ፣ በጭራሽ አታላግጥ ወይም በስድብ አትመልስላቸው። የእያንዳንዱን ሰው እራሱን የመግለጥ መብት አትፈታተን።

ስለ ሌሎች በመጥፎ መንገድ በጭራሽ አትናገር። ያወጣኸው አሉታዊ ኃይል ወደ አንተ ሲመለስ ይበዛል።

ሁሉም ሰው ይሳሳታል። እና ሁሉም ስህተቶች ይቅር ሊባሉ ይችላሉ።

መጥፎ አስተሳሰብ የአዕምሮ፣ የአካል እና የመንፈስ ህመም ያስከትላል። ብሩህ ተስፋን ተለማመድ።

የፍልስፍና ሀሁ መፅሐፍ